Fana: At a Speed of Life!

ራሽፎርድ፣ ሳንቾ፣ አንቶኒ፣ ጋርናቾ እና ማላሲያ ዩናይትድን መልቀቅ እንደሚፈልጉ አሳወቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ማርከስ ራሽፎርድ፣ ጀደን ሳንቾ፣ አንቶኒ ሳንቶስ፣ አሌሃንድሮ ጋርናቾ እና ታይረል ማላሲያ ማንቼስተር ዩናይትድን በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት መልቀቅ እንደሚፈልጉ አሳውቀዋል፡፡

ሁለቱ እንግሊዛዊያን የፊት መስመር ተጫዋቾች ራሽፎርድ እና ሳንቾ እንዲሁም አንቶኒ ከጥር ጀምሮ በውሰት ውል የውድድር ዓመቱን በተለያዩ ክለቦች አሳልፈዋል።

ራሽፎርድ በአስቶንቪላ፣ ሳንቾ በቼልሲ እንዲሁም አንቶኒ በሪያል ቤቲስ በውሰት ውል ቆይታቸው ጥሩ ጊዜን ማሳለፋቸው ይታወሳል፡፡

ራሽፎርድ በማንቼስተር ዩናይትድ ቤት ይለብሰው የነበረው 10 ቁጥር ማልያ ለአዲሱ ፈራሚ ማቲውስ ኩንሀ በዛሬው ዕለት ተሰጥቷል፡፡

ሌላው ቡድኑን መልቀቅ እንደሚፈልግ ያወቀው አርጀንቲናዊው ተጫዋች ጋርናቾ ከዩሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ በኋላ ከአሰልጣኝ ሩብን አሞሪም ጋር ግጭት ውስጥ ገብቶ እንደነበር ይታወቃል፡፡

አሰልጣኙም ከዚያ ጊዜ በኋላ ቡድኑን እንዲለቅ እና ክለብ እንዲፈልግ ነግረውት እንደነበር ይታወሳል፡፡

ከጉዳት ጋር በተያያዘ በሚገባው ልክ ቡድኑን እያገለገለ የማይገኘው ተከላካዩ ማላሲያ ቡድኑን መልቀቅ እንደሚፈልግ ያሳወቀ ሌኛው ተጫዋች ነው፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.