መሪዎች በተግባርም በሃሳብም መምራት መቻላቸው የመደመር ትውልድ መገለጫ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ተመስገን ጥሩነህ መሪዎች ሀገርን በተግባርም በሃሳብም መምራት መቻላቸው የመደመር ትውልድ መገለጫ ነው አሉ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት፤ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊነት ላይ ሆኖ መጽሐፍ መጻፍ ትልቅ ኃላፊነትና ትጋት የሚጠይቅ ተግባር ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለዚህ አረዓያና ተምሳሌት የሆኑ መሪ ናቸው ብለዋል፡፡
በተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የተፃፈውና “ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ፍለጋ” የተሰኘው መፅሀፍ የአዲሱ ትውልድ እሳቤን የሚያቀነቅን፣ የምንሸሻቸውን እና የደበቅናቸውን የራሳችንን ሀብቶች በድፍረት ገፍቶ ያወጣ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
መጽሐፉ እንድንጠይቅ፣ እንድንመረምር የሚያስገድደን እና ለተጨማሪ ክርክሮችና ሙግቶች በር የሚከፍት ስራ ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት በምክክር ችግሮቿን ለመፍታት ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ የጠቀሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከዚህ ወዲህ ችግሮችን በኃይል የመፍታት አባዜ ትውልዱ በቃ ሊለው ይገባል ነው ያሉት፡፡
ይህን መጽሐፍ ለእንደዚህ ዓይነቱ የሃሳብ ፍሰት ተጨማሪ ጉልበት እና ግብዓት አድርጎ መውሰድ እንደሚቻልም አስገንዝበዋል።
“ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ፍለጋ” ከተሰኘው መፅሀፍ የሚገኘው ገቢ ሐምሌ 2016 ዓ.ም በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚውል ይሆናል ተብሏል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!