“ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ፍለጋ” መጽሐፍ የዘመናት የዴሞክራሲ ፍለጋ ህልምን የሚዳስስ ነው – አቶ አደም ፋራህ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ “ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ፍለጋ” መጽሐፍ የኢትዮጵያ ህዝብን የዘመናት የዴሞክራሲ ፍለጋ ህልም የሚዳስስ የዕውቀት ብርሃን ነው አሉ፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የተጻፈው “ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ፍለጋ” መጽሐፍ ዛሬ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተመርቆ ለንባብ በቅቷል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ አቶ አደም ፋራህ እንደገለጹት፤ መጽሐፉ ኢትዮጵያዊ ባህል ወርቃማ የእሴት ቁልፎችን ይዟል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) አረዓያነት በመከተል መጽሐፍ የማዘጋጀት ሂደት ለሁሉም የስራ ኃላፊዎች ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን አብራርተዋል።
የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት ለትውልዶች ሲተላለፍ የቆየ ህዝባዊ ጥያቄ መሆኑን ገልፀው፤ ሁሉም ሲያውጠነጥነው የቆየና እስካሁንም የተሟላ ምላሽ ያልተገኘለት መሆኑን አንስተዋል።
መጽሐፉ ስለዴሞክራሲ የተከተልነውን አካሄድ እንድናጤንና በትኩረት እንድንሰራ የሚያግዘን ነው ብለዋል።
በዴሞክራሲ ላይ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት ሀገር በቀል እሴቶችን ከዘመናዊ አስተሳሰብ ጋር ማጣጣም፣ ኋላቀር የፖለቲካ ባህልን መቀየርና ሚዛናዊነትን ማጎልበት እንዲሁም የዴሞክራሲ ተቋማትን ማጠናከር ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
“ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ፍለጋ” መፅሐፍ ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን ማስረከብ የሚያስችል ምህዳር ለመፍጠር ጥብቅ ንድፈ ሀሳቦችን ማቅረቡን ተናግረዋል።
መጽሐፉ ለኢትዮጵያ ህዝብ የዘመናት የዴሞክራሲ ፍለጋ ህልም የዕውቀት ብርሃን መሆኑንም አስረድተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!