በአትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ ስኬት ላይ የሚያጠነጥን መጽሃፍ ለንባብ ሊበቃ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ ስኬት ላይ የሚያጠነጥነው DISSECTING HAILE (የኃይሌ ኃይሎች) የተሰኘው መፅሃፍ ለንባብ ሊበቃ ነው፡፡
መጽሃፉ በአትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ ልጅ ሜላት ኃይሌ የተጻፈ ሲሆን በመጪው ነሐሴ ወር በይፋ ይመረቃል ተብሏል።
መጽሃፉ ከሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ የስኬት ጀርባዎች ያሉ ፍልስፍናዎች እና መርሆችን የሚያትት መሆኑን የመፅሃፉ ደራሲ ሜላት ኃይሌ ገልጻለች።
የይቻላልን መንፈስ ከኃይሌ የህይወት ልምድ ሁሉም ሰው እንዲማር በማሰብ መፅሃፉን እንደጻፈችው ተናግራለች።
አስራ ሁለት ምዕራፎች ያሉት ሲሆን በአማርኛ እንግሊዘኛ ቋንቋዎች እንዲሁም በብሬል ተዘጋጅቷል።
መጽሃፉ ሲመረቅ በአማዞን፣ በቴሌብር እንዲሁም በተለያዩ የኦንላይን አማራጮችና የመፅሃፍ መደብሮች ለገበያ ይቀርባል።
በቅድስት ብርሃኑ