Fana: At a Speed of Life!

የብርሸለቆ መሠረታዊ የውትድርና ትምህርት ቤት ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አመራሮች እያስመረቀ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በመከላከያ ሰራዊት የምስራቅ ዕዝ በብርሸለቆ መሠረታዊ የውትድርና ትምህርት ቤት ለ2ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አመራሮች እያስመረቀ ነው።

በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል መሐመድ ተሰማን ጨምሮ የዕዙ ከፍተኛ መኮንኖችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በዛሬው እለት ለምርቃት የበቁት በዕዝ ሰንሰለቱ መሰረት ከጓድ መሪ እስከ ክፍለ ጦር አመራሮች መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በስልጠና ቆይታቸው የወታደራዊ ስነ-ልቦና ዝግጁነት፣ የአመራር ክህሎትና እውቀት እንዲሁም በቴክኖሎጂ የታገዙ ልዩ ልዩ ወታደራዊ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ወስደዋል ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.