Fana: At a Speed of Life!

ኢንተርፕራይዞችን በማበረታታት ወጣቱን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል – አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማፋጠን አምራች ኢንተርፕራይዞችን በማበረታታት ወጣቱን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል አሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ።
“የኢንተርፕራይዞች ሚና ለሀገራችን ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ በሀዋሳ ከተማ ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚካሄድ ክልላዊ ኤግዚቢሽንና ባዛር በዛሬው ዕለት ተከፍቷል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፥ የሀገር ምርትን ከፍ ማድረግ የውጪ ምንዛሪን ለማስቀረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አንስተዋል፡፡
በክልሉ ለወጣቶች የተለያዩ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር እና በማበረታታት ረገድ ባለፉት ዓመታት አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል ነው ያሉት፡፡
ሕብረተሰቡ ሀገር በቀል ምርቶችን በመጠቀም አምራች ኢንተርፕራይዞችን እንዲያበረታታም ጥሪ አቅርበዋል።
የክልሉ ሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሀገረፅዮን አበበ በበኩላቸው ፥ ባለፉት አምስት ዓመታት በዘርፉ ከ398 ሺህ በላይ ወጣቶች የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ጠቁመዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት 7 ሺህ ኢንተርፕራይዞች በክልሉ መኖራቸውን ጠቅሰው ፥ በአገልግሎት፣ በኢንዱስትሪ እና በግብርና ዘርፍ መሰማራታቸውን ተናግረዋል።
በነጻነት ሰለሞን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.