Fana: At a Speed of Life!

ቼልሲ ጄሚ ጊተንስን አስፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የቦሩሺያ ዶርትመንዱን የክንፍ ተጫዋች ጄሚ ጊተንስን አስፈርሟል፡፡
የ20 ዓመቱ ተጫዋች በ48 ነጥብ 5 ሚሊየን ፓውንድና በተጨማሪ 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ፓውንድ ለቼልሲ መፈረሙን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
እንግሊዛዊው ጊተንስ ለቦሩሺያ ዶርትመንድ በ107 ጨዋታዎች የተሰለፈ ሲሆን÷ በቆይታውም 17 ግቦችን በማስቆጠር 14 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል፡፡
ቼልሲ ቀደም ሲል የኢፕስዊች ታውኑን አጥቂ ሊያም ዴላፕ፣ የብራይተኑን ጆዓኦ ፔድሮ፣ የስፖርቲንግ ሊዝበኑን ዳሪዮ ዔሱጎ እንዲሁም የስትራስቡርጉን ተከላካይ ማማዱ ሳርን ማስፈረሙ ይታወቃል፡፡
በአቤል ንዋይ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.