ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከብራዚል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከብራዚል ፕሬዚዳንት ሉዊዝ ኢናቺዮ ሉላ ደ ሲልቫ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ ከ17ኛው የብሪክስ ጉባዔ አስቀድሞ ከብራዚል ፕሬዚዳንት ሉዊዝ ኢናቺዮ ሉላ ደ ሲልቫ ጋር ተወያይተናል ብለዋል፡፡
በውይይታቸውም በሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ነው የተናገሩት፡፡
የዛሬው ውይይት በቅርብ እያደገ የመጣውን የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር ረገድ አንድ ርምጃ ወደፊት የወሰደ ሆኗል ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ሁለቱ መሪዎች በተለያዩ ዘርፎች የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትስስሮችን ይበልጥ ለማጠናከርም ተስማምተዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡