Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ብልፅግና ፓርቲ የከፍተኛ አመራሮች መድረክ ቀጥሎ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ብልፅግና ፓርቲ የከፍተኛ አመራሮች መድረክ በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳይች ላይ በባህርዳር ከተማ እያካሄደው ያለው መድረክ እንደቀጠለ መሆኑን ፓርቲው አስታወቀ።

መድረኩን በተመለከተ እንደተጠናቀቀ አጠቃላይ መረጃ የሚሰጥ መሆኑንም የአማራ ብልፅግና ፓርታ ጽህፈት ቤት ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

ሆኖም ግን በአንዳንድ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ከመድረኩ ባህሪና ነባራዊ ሁኔታ ባፈነገጠ መንገድ የተዛቡ መረጃወች እየተዘዋወሩ መሆኑንም አስገዝንቧል።

ለአብነት ያህል “በመድረኩ አመራሩ ለሁለት ተከፍሏል” የሚሉና አመራሮቹን በስም በመጥራት እገሌ ይህንን ብለዋል በሚል የተለቀቁ የሀሰት መረጃወች ይገኙበታል ብሏል ጽህፈት ቤቱ።

በመሆኑም መረጃወቹ ከእውነት የራቁ መሆኑን ያስታወቀው ጽህፈት ቤተ፥ በመድረኩ የሚደረሱ ድምዳሜወችንና የፓርቲውን አቋም የግምገማ መድረኩ እንደተጠናቀቀ እንደሚያደርስም አስታውቋል።

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በክልሉና በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በባሕር ዳር እያደረጉት ያለው ስብሰባ ከትናንት ጀምሮ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል።

የውይይት መድረኩ በለውጥ ሂደቱ የተመዘገቡ ውጤቶችና ያጋጠሙ ፈተናዎችን በመለየት የመፍትሄ እርምጃዎችን ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑንም ተገልጿል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.