Fana: At a Speed of Life!

ተረጂነትን ማስቀረትና የተጎዱ ወገኖቻችንን በራስ አቅም መደገፍ የሉዓላዊነት ጉዳይ ነው – ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ተረጂነትን ለማስቀረትና የተጎዱ ወገኖቻችንን በራስ አቅም መደገፍ የሉዓላዊነት ጉዳይ አድርገን ማሰብ አለብን አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ፡፡
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓል “90 ዓመታትን የተሻገረ የሰብዓዊ አገልግሎት አሻራ” በሚል መሪ ሀሳብ በዛሬው ዕለት ተከብሯል።
የማህበሩ የበላይ ጠባቂ የሆኑት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፥ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በኢትዮጵያ ፈተናዎች የተወለደ የርህራሄና የበጎነት መገለጫ ነው ብለዋል።
ማህበሩ ባለፉት 90 ዓመታት ኢትዮጵያ ችግር ላይ በነበረችበት ወቅት ሁሉ ላከናወናቸው ሰብዓዊና የጀግንነት ተግባራት በኢትዮጵያ መንግስት ስም ምስጋና አቅርበዋል።
በራስ አቅም የተመሰረተ ሰብዓዊ አሻራን ለማኖር ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ያስገነዘቡት፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ በምግብ ራስን ለመቻል፣ በኢኖቬሽን ራሳችንን ለማብቃት ቀን ከሌሊት እንደምንተጋው ሁሉ ተረጂነትን ለማስቀረትና የተጎዱ ወገኖቻችንን በራስ አቅም መደገፍ የሉዓላዊነት ጉዳይ አድርገን ማሰብ አለብን ብለዋል።
ለዚህም ከነባራዊው የእርዳታ ጥገኝነት በመላቀቅ የሰብዓዊ ተግባራትን በራስ አቅም የሚያሟላ ቁመና መገንባት እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.