Fana: At a Speed of Life!

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አብሮነትን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ዜጎች በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በተለያዩ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ሕብረተሰቡን በማሳተፍ ተጀምሯል፡፡

አገልግሎቱ የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት በማደስ፣ በአረንጓዴ አሻራ፣ በደም ልገሳ፣ በትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ፣ በነጻ ሕክምና፣ በማዕድ ማጋራትና በተለያዩ በጎ ሥራዎች ነው እየተከናወነ የሚገኘው፡፡

አቶ አደም ፋራህ እንዳሉት÷ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የዜጎችን አብሮነት፣ መተሳሰብ፣ ሁለንተናዊ ትብብርና መተጋገዝ ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡

ባለፉት ዓመታት በበጎ ፈቃድ ተግባራት በተከናወኑ ሥራዎች ለሀገር ልማት እና ዕድገት ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን አስታውሰዋል፡፡

በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትም ሕብረተሰቡ በንቃት በመሳተፍ የሚጠበቅበትን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተለይም ወጣቶች የመርሐ ግብሩ የጀርባ አጥንት መሆናቸውን ጠቅሰው÷ ስኬታማ ሥራ ለማከናወን በሃላፊነት እንዲንቀሳቀሱ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ድንበር ተሻጋሪ መሆን እንዳለበት የተናገሩት አቶ አደም÷ይህም ሕብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት የተጀመረውን ጥረት ያጠናክራል ነው ያሉት፡፡

በመላኩ ገድፍ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.