Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ እያከናወነች ያለው ተግባር አስደናቂ ነው – የተለያዩ ሀገራት ሚኒስትሮች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ዕድገቷን ለማፋጠን በቴክኖሎጂ ዘርፍ እያከናወነች ያለው ተግባር አስደናቂና ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ልምድ የሚሆን ነው አሉ በ3ኛው የአፍሪካ የሥራ ፈጠራ ፎረም ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት ሚኒስትሮች፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 3ኛው የአፍሪካ የሥራ ፈጠራ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የዘርፉ ምሁራን፣ ተመራማሪዎች፣ ሥራ ፈጣሪዎች እና የዓለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ የዓድዋ ድል መታሰቢያን፣ ሳይንስ ሙዚዬምንና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡

በጉብኝቱ ወቅት አስተያየታቸውን የሰጡት ተሳታፊዎቹ÷ አዲስ አበባ በፈጣን ዕድገት ላይ መሆኗን መመልከታቸውን ተናግረዋል።

የመሰረተ ልማት ግንባታዎቹ የከተማዋን እድገት የሚያፋጥኑ መሆናቸውን ገልጸው÷ ኢትዮጵያ እድገቷን ለማፋጠን የጀመረቻቸው ተግባራት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ምሳሌ ናቸው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የጀመረቻቸው ተግባራት በአፍሪካ ከምግብ ዋስትና ጋር ተያይዘው የሚነሱ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ መሆናቸውን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሀገራት ተሞክሮ የሚሆን የልማት ሥራ እያከናወነች መሆኑን የጠቀሱት ተሳታፊዎቹ÷ ተግባራቱ ኢትዮጵያን በዘርፉ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሀገር ያደርጋታል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.