Fana: At a Speed of Life!

የሐረር ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራ ለሌሎችም ተሞክሮ የሚሆን ነው – የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረር ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ሥራ ለሌሎችም ተሞክሮ የሚሆን ነው አሉ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች።

ከብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤትና ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ የዴሞክራሲ ባሕል ግንባታ ዘርፍ አመራሮች በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

በዚህም የሐረርን የኮሪደር ልማት፣ ዓለም አቀፉ የጁገል ቅርስ የኮሪደር መልሶ ልማት፣ የወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ግንባታዎችና ሌሎች ሥራዎችን ተመልክተዋል፡፡

አመራሮቹ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በሐረር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች አበረታችና የከተማዋን የቀድሞ ምልከታ የቀየሩ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

የኮሪደር ልማት ሥራው በሐረር ከተማ ለነዋሪዎች ምቹ የመኖሪያ እና የመዝናኛ አካባቢ መፍጠር ማስቻሉን ነው ያስረዱት፡፡

ልማቱ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ መጠቀሱንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

በተለይ በዓለም አቀፉ የጁገል ቅርስ የተከናወነው የኮሪደር መልሶ ልማት ሥፍራውን ለኑሮ ምቹ በማድረግ ቅርሱ ሕያውነቱን ጠብቆ እንዲቀጥል አስችሏል ነው ያሉት አመራሮቹ፡፡

ልማቱ የአካባቢ ጸጋና ሀገር በቀል እውቀትን ተጠቅሞ በአነስተኛ ዋጋ መከናወኑ ደግሞ ለሌሎች አካባቢዎች ተሞክሮ የሚሆንና ትምህርት የሚወሰድበት መሆኑንም አስገንዝበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.