ሠራዊቱ ሰላሙን እያስጠበቀ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መስጠቱ ምሉዕ ያደርገዋል – ሌ/ጄ ዘውዱ በላይ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሠራዊቱ ሰላሙን እያስጠበቀ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መስጠቱ ምሉዕ ያደርገዋል አሉ የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ።
ዕዙ ለተከታታይ 12 ቀናት ሲያካሄድ የነበረው የ2017 ዓ.ም ስፖርታዊ ፌስቲቫል ሌተናል ጄነራል ዘውዱ በላይን ጨምሮ የጅማ ዞንና ጅማ ከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።
የፌስቲቫሉን መጠናቀቅ ተከትሎ የሠራዊቱ አባላት የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናውነዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ፤ የፕሮፌሽናል ሠራዊት ግንባታ ማበልጸጊያ አንዱ ማህበረሰቡን ከልብ እንደ ልብ ማገልገል ነው ብለዋል።
ማንኛውም የሠራዊት አባል ሰላሙን እያስጠበቀ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መስጠቱ ይበልጥ ምሉዕ ያደርገዋል ነው ያሉት።
የደም ልገሳን ጨምሮ የተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን ሠራዊቱ በመደበኛነት እንደሚሰጥም አረጋግጠዋል።
በአብዱረህማን መሀመድ