Fana: At a Speed of Life!

131 ሺህ 14 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በ2017 በጀት ዓመት 131 ሺህ 14 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል አለ፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው የዓመቱን ዲፕሎማሲያዊ ተግባራት እና ሳምንታዊ ክንውኖች አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለ968 የጎረቤት ሀገራት ተማሪዎች ነፃ የከፍተኛ ትምህርት እድል ተሰጥቷል ብለዋል።

ይህም ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ትስስርን ለማጠናከር ከምታከናውናቸው ተግባራት መካከል መሆኑን ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ 131 ሺህ 14 ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉንና በሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰዋል።

በበጀት ዓመቱ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ 198 ስምምነቶች መፈጸማቸውንም ነው አምባሳደር ነብያት የጠቆሙት።

በአሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.