Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም እየተገመገመ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአዳማ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በመድረኩ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የግምገማ መድረኩ በክልሉ የ2017 በጀት ዓመት የመንግሥት እና የፓርቲ ሥራ አፋጻጸም ላይ እንደሚያተኩር
ተመላክቷል፡፡
ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ በ2017 በጀት ዓመት ያጋጠሙ በርካታ ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር ዓመቱን በስኬት ማጠናቀቅ ተችሏል፡፡
በበጀት ዓመቱ እንደ ክልል መንግስትም ሆነ እንደ ፓርቲ የነበሩ ክፍተቶችን በ2018 ዓ.ም ለማስተካከል በትኩረት እንደሚሰራ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በመድረኩ በተጠናቀቀው ዓመት የችግር ምንጭ የነበሩ ጉዳዮችን በመፈተሽ የመፍትሔ አቅጣጫ እንደሚቀመጥ መጠቀሱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡
በአቤል ንዋይ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.