Fana: At a Speed of Life!

አንድ ኢትዮጵያ የባሕል ቡድን የፋና 80 የዳንስ ውድድር አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ላለፉት ዘጠኝ ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው የፋና 80 ምዕራፍ 3 የዳንስ ውድድር በዛሬው ዕለት ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡

በምዕራፍ 3 ውድድር 16 የዘመናዊና የባህላዊ ዳንስ ቡድኖች የተሳተፉ ሲሆን÷ ዛሬ በተካሄደው የፍጻሜ ውድድር አራት ቡድኖች ተሳትፈዋል፡፡

በፍጻሜው ጊዮን፣ ነገስታት እና ጥያቄ የተሰኙ ዘመናዊ የዳንስ ቡድኖች እንዲሁም አንድ ኢትዮጵያ የባህል ቡድን በሁለት ዙር ሥራዎቻቸውን በማቅረብ ብርቱ ፉክክር አድርገዋል፡፡

በዚህ መሰረትም አንድ ኢትዮጵያ የባህል ቡድን የፋና 80 ምዕራፍ 3 የዳንስ ውድድርን በማሸነፍ የ200 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡

በተጨማሪም ነገስታት ዘመናዊ የዳንስ ቡድን 2ኛ ደረጃን በመያዝ 150 ሺህ ብር የተሸለመ ሲሆን ÷ ጥያቄ ዘመናዊ የዳንስ ቡድን 3ኛ እና ጊዮን ዘመናዊ የዳንስ ቡድን ደግሞ 4ኛ በመውጣት በቅደም ተከተል የ100 ሺህ እና የ70 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

አራቱም ቡድኖች በቀጣይ በሚካሄደው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በቀጥታ የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.