Fana: At a Speed of Life!

በእስራኤል ጥቃት መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው የኢራን ፕሬዚዳንት…

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢራን ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን እስራኤል ባሳለፍነው ሰኔ 8 በፈጸመችው የአየር ጥቃት መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በቴህራን የከፍተኛ ደረጃ የፀጥታ ስብሰባ ላይ በነበሩበት ወቅት እስራኤል በፈጸመችው የአየር ጥቃት መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ነው የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣን የተናገሩት።

ጥቃቱ በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ላይ ያነጣጠረ የነበረ ሲሆን፥ ነገር ግን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ከጥቃት መጠነኛ ጉዳት ብቻ አስተናግደው ማምለጣቸውን ተመልክቷል።

በስድስት ሚሳኤሎች ህንፃውን በመምታት ኃይል እንዲቋረጥ እና መውጫዎችን እንዲዘጉ በማድረግ በተፈጸመው በዚህ ጥቃት ፕሬዚዳንቱ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ማምለጥ ችለዋል።

ጥቃቱ የደረሰው በእስራኤል እና በኢራን መካከል ለ12 ቀናት በዘለቀው ጦርነት ወቅት ሲሆን፥ኢራን ከጥቃቱ ጀርባ ያሉ ሰላዮችን እየመረመረች ትገኛለች ሲል የዘገበው አልጀዚራ ነው።

በዮናስ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.