ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6 ፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላፉት የሃዘን መግለጫ ፥በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ ስም ለሙሃማዱ ቡሃሪ ቤተሰብ፣ ለናይጄሪያ ሕዝብ እና መንግስት መጽናናትን ተመኝተዋል።