ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት ተከናውነዋል – ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በራስ ፀጋ የምግብ ሉዓላዊነትን እንዲሁም ሁለንተናዊ እድገትና ብልጽግናን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተከናውነዋል አሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በመንግስት እና በፓርቲ ትብብር የተከናወኑ አበይት ተግባራትን የሚገመግም መድረክ በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው።
ከተረጅነት የመውጣት ጥረት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የገበያ ማረጋጋትና የኑሮ ውድነትን በመቀነስ ረገድና ሌሎች ጉዳዮችን በመዳሰስ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትና የተመዘገቡ ውጤቶችን በተመለከተ በስፋት ውይይት ተደርጓል።
በዚሁ ጉዳይ ማብራሪያ የሰጡት ሚኒስትራ፤ ለዜጎች በውጭና የሀገር ውስጥ የሥራ ዕድል በማመቻቸትና በመፍጠር ረገድ የተሳካ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲኖር በማድረግ ዜጎች በቀሰሙት ዕውቀትና ክህሎት ለሀገር ከፍታና ብልፅግና መረጋገጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
ከሥራ ዕድል ፈጠራ ባሻገር በሌሎች ዘርፎችም ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን አንስተው÷ የምግብ ሉዓላዊነትን እንዲሁም ሁለንተናዊ እድገትና ብልጽግናን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተከናውነዋል ነው ያሉት።
የተመዘገበውን ውጤት ለማጽናትም የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!