የቼልሲው ግብ ጠባቂ ፔትሮቪች ለቦርንማውዝ ፈረመ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ግብ ጠባቂ ጆርጄ ፔትሮቭች በ25 ሚሊየን ፓውንድ ለቦርንማውዝ ፈረመ፡፡
በፈረንጆቹ 2023 ከኒው ኢንግላንድ ሪቮሉሽን በ14 ሚሊየን ፓወንድ ሰማያዊዎቹን የተቀላቀለው ሰርቢያዊው ግብ ጠባቂ፤ በተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን ለፈረንሳዩ ክለብ ስትራስቡርግ በውሰት መጫወቱ ይታወሳል።
የ25 አመቱ ፔትሮቪች ለቦርንማውዝ የክረምቱ ሶስተኛ ፈራሚ ሲሆን የ5 ዓመት ኮንትራት ውል ገብቷል።
ፔትሮቪች በሁለት አመት የቼልሲ ቤት ቆይታው 23 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡
ቦርንማውዝ ቋሚ ግብ ጠባቂውን ስፔናዊው ኬፓ አሪዝባላጋን ለአርሰናል መሸጡን ተከትሎ ፔትሮቪች ሁነኛ ተተኪ እንደሚሆን በማመን ያስፈረመው መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በአቤል ንዋይ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡