Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ሃይል ስብሰባ ላይ በሞቃዲሾ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሞቃዲሾ እየተካሄደ በሚገኘው 34ኛው የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ሃይል ፖሊሲ አካላት ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው

በመድረኩ የሁሉም አባል ሀገራት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሞች፣ የመከላከያ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ ኤክስፐርቶች ተሳትፈዋል፡፡

የመከላከያ ውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክተር ሜ/ጄ ተሾመ ገመቹ የተመራ ልዑክም የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን በመወከል እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

በስብሰባው አባል ሀገራቱ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ላይ የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ሃይል ሊኖረው በሚገባው ጉልህ አስተዋፅኦ ዙሪያ በትኩረት እየመከሩ ነው፡፡

በተጨማሪም የድርጅቱ የአምስት ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድና በቀጣይ ጅቡቲ ላይ እንደሚካሄድ በሚጠበቀው የባህር ኃይል ኮማንድ ፖስት ስልጠና ዕቅድ ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡

ድርጅቱ ከምስረታው ጀምሮ የነበረውን ሒደት የሚያሳይ ጥናት ላይ ምክክር እንደሚካሄድም የመከላከያ ሠራዊት ኦንላይን ሚዲያ ዋና አዘጋጅ ሌ/ኮ ውብሸት ቸኮል ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።

በመላኩ ገድፍ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.