Fana: At a Speed of Life!

የአረንጓዴ አሻራ ስራ ባህርዳር ከተማን ምቹ ዓለም አቀፍ መዳረሻ የሚያረጋት ይሆናል – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የአረንጓዴ አሻራ ስራ ባህርዳር ከተማን ምቹ ዓለም አቀፍ መዳረሻ የሚያረጋት ይሆናል አሉ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በመትከል ማንሰራራት ጉዞ ላይ ነን ብለዋል።

ዛሬ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ለመጪው ትውልድ አረንጓዴ ሀገር ለማስረከብ ከሀገር ተረካቢ ታዳጊዎች፣ ወጣቶች፣ የክልሉ እና የባህርዳር ከተማ ከፍተኛ አመራሮች ጋር የአረንጓዴ አሻራችንን አኑረናል ሲሉ ገልጸዋል።

የአረንጓዴ አሻራችን እንደሀገር የውበት ምንጭ የኢኮኖሚ ተደማሪ አቅም ይሆናል ብለን አቅደን የሰራነው በውጤት ፍሬ አፍርቶ እየታየ ነው ብለዋል።

በባህርዳርም የአረንጓዴ አሻራ ስራ በዘንባባዎች እና በልምላሜዎቿ የተዋበችውን ከተማ ይበልጥ የተዋበች እና ምቹ ዓለም አቀፍ መዳረሻ የሚያረጋት ይሆናል ነው ያሉት።

ለሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራችን በተባበረ ክንድ እንትጋ ሲሉም ጥሪ አስተላልፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.