የአፋር ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፋር ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል።
በጉባኤው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ የ2017 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርትን ለምክር ቤቱ አባላት እያቀረቡ ይገኛሉ።
ርዕሰ መስተዳደሩ በሪፖርታቸው፤ ሰላም እና ጸጥታ በተመለከተ በክልሉ በተሰራው ስራ ሰላምን ለማጽናት የሚያስችል ውጤት ተገኝቷል ብለዋል።
የምክር ቤቱ ጉባዔ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይወያያል።
እንዲሁም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ክንውንና የዋና ኦዲተርን የስራ ሪፖርት የሚያደምጥ ሲሆን፤ የ2018 በጀትን ጨምሮ የተለያዩ አዋጆችን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በካሊፋ ከድር