Fana: At a Speed of Life!

ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን የዕውቅናና የሽልማት መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በናይጄሪያ አቡኩታ ከተማ በተካሄደው የአፍሪካ ከ20 እና 18 ዓመት በታች ሻምፒዮና ላይ ተሳታፊ ለነበሩት አትሌቶችና የቡድን አባላት የእውቅናና ሽልማት መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡
በውድድሩ ለተሳተፉ እና ሜዳሊያ ላስገኙ አትሌቶች፣ ለአሰልጣኞች፣ ለቡድን መሪ እና ለልዑካን ቡድኑ አባላት የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ኢትዮጵያን በመወከል በውድድሩ በዳኝነት የተሳተፈው ኢንስትራክተር ሳሙኤል ብርሃኑ የዕውቅና እና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶለታል።
በሽልማትና በዕውቅና መርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አትሌት ስለሺ ስህንን ጨምሮ ሌሎችም የፌዴሬሽኑ አመራሮች ተገኝተዋል።
በሁለቱም የእድሜ እርከን ውድድሮች ላይ በ28 አትሌቶች የተካፈለችው ኢትዮጵያ 2 የወርቅ፣ 3 የብር እና 5 የነሃስ ሜዳልያዎችን ማስመዝገቧ ይታወሳል።
ከሐምሌ 9 እስከ ሐምሌ በናይጄሪያ አቡኩታ በተካሄደው ሻምፒዮና ላይ የተሳተፉ አትሌቶች ትናንት ምሽት ወደ ሀገር ቤት ሲመለሱ አቀባበል እንደተደረገላቸው ይታወሳል፡፡
በእንዳልካቸው ወዳጄ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.