Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ትዕግስት አሰፋ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ትወክላለች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አትሌት ትዕግስት አሰፋ በጃፓን ቶኪዮ በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን በመወከል ትወዳደራለች።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከአሠልጣኟ ጋር ባደረገው ውይይት አትሌት ትዕግስት በዓለም ሻምፒዮና ላይ ሀገሯን በመወከል እንድትሳተፍ ከስምምነት ላይ መደረሱን ገልጿል።

በአሁኑ ስዓት አትሌቷ በጥሩ አቋም ላይ በመሆኗ ክብረወሰን በማሻሻል የኢትዮጵያ ስም ከፍ ለማድረግ በማሰብ ጥሪውን መቀበሏን አሠልጣኟ ገመዶ ደደፎ ተናግረዋል፡፡

የፓሪስ ኦሎምፒክ የብር ሜዳልያ የለንደን ማራቶን አሸናፊዋ ትዕግስት አሰፋ በሻምፒዮናው ላይ እንድትሳተፍ ለቀረበላት ጥያቄ ለሰጠችው በጎ ምላሽ ፌዴሬሽኑ ምስጋና አቅርቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.