Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ኔዘርላንድስ በዜግነት አገልግሎት ዘርፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ኔዘርላንድስ በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ተስማምተዋል።

በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የተመራ እና ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጣ የስራ ሀላፊዎችን ያካተተ የልዕካን ቡድን በኔዘርላንድስ የስራ ጉብኝት አካሂዷል።

ጉብኝቱ በዋናነት በሀገራቱ መካከል ጸንቶ የቆየውን ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነትና ትብብር ከማጠናከር ባሻገር በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዘርፍ፣ በድንበር እና በማቆያ ማዕከላት አስተዳደር እንዲሁም ከስደተኞችና ተመላሾች ዘርፍ ያሉ መልካም ተሞክሮዎችን ለመቅሰም ያለመ ነው።

በዚህም ልዑኩ በሀገሪቱ የተለያዩ ተቋማትን በመጎብኘት ዘርፉን ከሚመሩ የስራ ሃላፊዎች ጋር ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት ማካሄዱን ኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ አመልክቷል።

የኔዘርላንድስ የኢሚግሬሽን ተቋም ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ቡድን ባለፈው የካቲት ወር ላይ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ማድረጉ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.