የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አመርቂ ድሎችን አስመዝግቧል – ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ሰላምና ደህንነትን ከማረጋገጥ አኳያ አመርቂ ድሎች ተመዝግበዋል አሉ፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2018 በጀት ዓመት ሀገራዊ ዕቅድና በተቋሙ የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው።
ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ተቋሙ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ውጤታማ ስራዎችን አከናውኗል፡፡
የአምስት ዓመቱ የስትራቴጂክ ዕቅድ አፈጻጸሙም ስኬታማ መሆኑን አንስተው፤ በመጪዎቹ አምስት ዓመታትም ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ፣ ዲፕሎማሲ፣ በጸጥታ፣ በዲጂታል እና በሌሎችም ዘርፎች አመርቂ ድሎችን አስመዝግባለች ነው ያሉት፡፡
ለድሎቹ መገኘትም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሰላምና ደህንነትን ከማረጋገጥ አኳያ በርካታ ድሎችን ማስመዝገቡን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በቀጣይም ሀገራዊ የልማት ዕቅዶች በውጤታማነት እንዲከናወኑ ኮሚሽኑ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት እንደሚወጣ ተናግረዋል።