ቪክተር ጎከሬሽ የአርሰናል ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ወደ ለንደን ሊያቀና ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሰናል ቪክተር ጎከሬሽን ከስፖርቲንግ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ መድረሱን ተከትሎ ተጫዋቹ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ነገ ወደ ለንደን እንደሚያቀና ተነግሯል፡፡
አርሰናል ለ27 ዓመቱ ስዊድናዊ አጥቂ ዝውውር 55 ነጥብ 1 ሚሊየን ፓውንድ እና ብቃቱ እየታየ የሚጨመር 8 ነጥብ 7 ሚሊየን ፓውንድ ይከፍላል፡፡
ተጫዋቹ የህክምና ምርመራውን ካጠናቀቀ በኋላ በሲንጋፖር በቅድመ የውድድር ዘመን ዝግጅት ላይ የሚገኘውን የሚኬል አርቴታ ስብስብ በይፋ እንደሚቀላቀል ስካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡