Fana: At a Speed of Life!

የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በፓኪስታን በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ‘በመትከል ማንሠራራት’ የ2017 የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት በፓኪስታን ኢስላምአባድ በይፋ ተጀምሯል።

በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሀገሪቱ የምግብ ደህንነትና ምርምር ሚኒስቴርና ብሄራዊ የግብርና ምርምር ማዕከል ጋር በመተባበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ፎረም አካሂዷል።

ከፎረሙ በመቀጠል በምርምር ማዕከሉ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡

በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) በፎረሙ ላይ እንደገለጹት፥ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡

የሚኒስቴሩ ፀሐፊ አሚር ሞህዩዲን በበኩላቸው፥ ሀገራቸው የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ ተነሣሽነት በፓሊሲ ደረጃ ቀርጻ እንደምታከናውን ተናግረዋል።

ዛሬ የተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በሌሎች ከተሞችም እንደሚቀጥል ኤምባሲው ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ አመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.