Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደርን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 7 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር በመሆን የተሾሙት ጀማል ኢል ሸኪ የሹመት ደብዳቤ ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለዋል።

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በዚህ ወቅት እንደተናገሩት÷ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ዘመናትን ያስቆጠረና በብዙ መልኩ የሚገለጽ በወንድማማችነትና በወዳጀነት ላይ የተመሰረተ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የሁለቱን አገራት ዘላቂ ጥቅምና ፍላጎት ባስጠበቀ መልኩ ለዘመናት የቆየውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትሰራለችም ነው ያሉት።

አያይዘውም አምባሳደር ጀማል ኢል ሸኪ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ለሥራቸው መቃናት የኢትዮጵያ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደረግላቸው በመግለጽ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን ገልጸዋል።

አምባሳደር ጀማል ኢል ሸኪ በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ግዜ ተሹመው መምጣታቸውን በማስታወስ፣ የረጅም ዘመናት የባህል፣ የታሪክና የአስተሳሰብ ትስስር ያላቸውን ወንድማማች ህዝቦች በአምባሳደርነት ለማገልገል በመምጣታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

በቆይታቸውም የሁሉቱን አገራት ግንኙነት በሁሉም ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸውን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.