የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ጀሲካ አሊፖ በኢትዮጵያ በሚካሄደው በሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ሥርዓት ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ምክትል ፕሬዚዳንቷ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት መረጃ ያሳያል።
ኢትዮጵያ ከሐምሌ 20 እስከ 22 ቀን 2017 ዓ.ም የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤን በአዲስ አበባ ታስተናግዳለች።
ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ስኬቶችን በማስመዝገብ የማንሰራራት ጉዞን በጀመረችበት ወቅት በምታስተናግደው በዚህ ጉባኤ፤ በበጋ መስኖ ስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በአረንጓዴ ዐሻራ ያስመዘገበችውን ስኬታማ ድሎ በተሞክሮነት ታቀርባለች ተብሎ ይጠበቃል።