Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ምክር ቤት ከ225 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት የክልሉን የ2018 በጀት ዓመት ጥቅል በጀት ከ225 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ በማድረግ አጽድቋል፡፡

ምክር ቤቱ በ6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባዔ የአራተኛ ቀን ውሎው ነው የክልሉን ጥቅል በጀት ያጸደቀው፡፡

የክልሉ የገንዘብ ቢሮ ኃላፊ ጥላሁን መሀሪ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንደገለጹት፥ የሕዝብ አንገብጋቢ ችግሮችን ታሳቢ ያደረገ የካፒታል በጀት ድልድል ተደርጓል፡፡

የበጀት ድልድሉ የወጪ ፍላጎትን እንዲሁም የቢሮዎችን፣ የወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮችን ድርሻ በመወሰን ፍትሕዊነትን ታሳቢ ያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የድህነት ተኮር ሴክተሮች የበጀት ድርሻቸው የተሻለ እንዲሆን የዓለም አቀፍ ስምምነቶችንና ሀገራዊ አቅጣጫዎችን ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው መባሉን አሚኮ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.