Fana: At a Speed of Life!

የቤተመንግሥቱ ዕድሳት መንግስት ለቅርሶች ጥበቃ የሰጠውን ልዩ ትኩረት የሚያሳይ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአጼ ፋሲል ቤተመንግሥት የዕድሳትና ጥገና ስራ መንግስት ለባህላዊ ቅርሶች ጥበቃና ልማት የሰጠውን ልዩ ትኩረት የሚያሳይ ነው አሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴርና የክልልና የከተማ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት የጎንደር ከተማን የኮሪደር ልማትና የአጼ ፋሲል አብያተ መንግስት እድሳትን ጎብኝተዋል።

ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ የቅርስ ጥገና ስራው ቅርስን ከጥበብ ጋር ያገናኘ እንዲሁም የሀገርን ሃብት ጠብቆ የማቆየትና ለትውልድ የማስተላለፍ ዘመን ተሻጋሪ ታሪካዊ አሻራ ነው።

ጎንደር የጥበበኞች የታዋቂ ከያንያንና አርቲስቶች መፍለቂያ መሆኗን ጠቅሰው፥ ትርክት የሚገነባው በጥበብ በመሆኑ መንግስት ለባህል ልማት ዘርፍ የሰጠው ትኩረት በጥበቡ ዘርፍ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑንም አንስተዋል።

የኮሪደር ልማት ስራውም የጎንደርን ታሪካዊነት ከጽዳት፣ ከምቾትና ከውበት ጋር ያጣመረ ድንቅ ስራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በጉብኝቱ የተሳተፉ አመራሮች በበኩላቸው፥ የተመለከቷቸው የልማት ስራዎች የልምድ ልውውጥ ለማካሄድና ተሞክሮን ለማካፈል ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ነው ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.