የክልሉ ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አባላት ቁጥር 421 ሺህ ደረሰ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ጤና ቢሮ በክልሉ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አባላትን ቁጥር ከ421 ሺህ በላይ ሆኗል አለ።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በ2017 በጀት ዓመት የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባላትን ወደ 557 ሺህ 412 ለማድረስ ታቅዶ በተሰራው ስራ 421 ሺህ 541 አባላት ማፍራት ተችሏል።
በዚህም የአባላት ምጣኔ ሽፋኑ 75 ነጥብ 62 በመቶ መድረሱን ገልጸው÷ የጤና መድኅን ተጠቃሚዎችን እርካታ ለማሻሻል በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
በበጀት ዓመቱ 289 ሺህ 696 ነባር አባላት እድሳት ለማከናወን ታቅዶ 258 ሺህ 776 በማሳካት የዕቅዱን 89 ነጥብ 3 በመቶ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል።
በበጀት ዓመቱ የተሰራው ስራ የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን አንስተው፥ በአዲሱ በጀት ዓመት የአባላት ቁጥር ለመጨመርና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት።
በክልሉ አሁን ላይ 2 ሚሊየን 65 ሺህ 550 ሕዝብ የጤና መድኅን አገልግሎት ተጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል።
በተጨማሪም የቅድመ ቁርጥ ክፍያ በክልሉ ሁሉም ጤና ተቋማት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በማድረግ ከ139 ሚሊየን ብር በላይ ለመድኃኒት ግዥ ለቀጣይ ስድስት ወራት እንዲውል ማስተላለፍ መቻሉን ጠቁመዋል።
ገቢን መሠረት ያደረገ ክፍያ ተግባራዊ ማድረግ እንዲሁም በክልሉ ሁሉም ዞኖች የገንዘብ ቋት እንዲኖር የሚሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን 445 ሚሊየን 736 ሺህ 763 ብር ተሰብስቦ ወደ ባንክ መግባቱን ገልጸው÷ ከዚህም ገንዘብ 139 ሚሊየን 544 ሺህ 607 ብር ወደ ጤና ተቋም ተላልፎ የመድኃኒት ግዥ መፈጸሙን አመልክተዋል።
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!