በዛሬው ዕለት በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኞች ይተከላሉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት 700 ሚሊየን ችግኞች ይተከላሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመላ ሀገሪቱ የሚካሄደውን የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፥ መርሐ ግብሩ ጥንካሬያችንን፣ አንድነታችንንና ለሕዝባችን ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።
ኢትዮጵያ አረንጓዴና ለፈተና የማይበገር ነገዋን ለመገንባት ለምታደርገው ጥረት እንደገና ትነሳለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በመርሐ ግብሩ ላይ በመሳተፍ በጋራ ታሪክ እንስራ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡