Fana: At a Speed of Life!

በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኝ መትከል በዓለም ትልቁ ውጤት ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኝ መትከል በዓለም ትልቁ የአንድ ቀን ተከላ ውጤት ነው አሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጅማ ዞን አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር የዘንድሮውን የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 8 ቢሊየን ገደማ ችግኞች የሚተከሉ ሲሆን፥ ይህም ባለፉት ሰባት ዓመታት የተተከሉ ችግኞችን መጠን 48 ቢሊየን ማድረስ የሚያስችል ነው፡፡

በአረንጓዴ አሻራ ዕቅዳችን 50 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ይህ ኢትዮጵያ ትላልቅ ነገር አቅዳ መስራት እንደምትችል ማሳያ እንደሆነ አንስተዋል፡፡

ዜጎቻችን አብሮ መስራትንና ትርፋማ መሆንን ስለሚያልሙ በዚህ ታሪካዊ ስራ ላይ አሻራቸውን እያሳረፉ እንደሆነ ጠቅሰው፥ በአረንጓዴ አሻራ ብዙ ትርፍ አግኝተናል፣ ምግባችንን ከጎሯችን አግኝተናል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ታሪክ ይቀየራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የዚህ ታሪክ አካል ለመሆን መላው ኢትዮጵያዊ በዛሬው ዕለት አሻራውን እንዲያኖር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዘንድሮው የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር 700 ሚሊየን ችግኞች የመትከል መርሐ ግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.