Fana: At a Speed of Life!

በአረንጓዴ አሻራ ዓለምን የሚያስደምም ስራ እየሰራን ነው – ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዓለምን የሚያስደምም ስራ እየሰራን ነው አሉ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር ላይ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

ከንቲባዋ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ አረንጓዴ አሻራ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና አዲስ አበባን አረንጓዴ ለማልበስ እንዲሁም ለነዋሪዎቻችን ምቹ ለማድረግ ትልቅ ጠቀሜታ አለው፡፡

ማህበረሰባችን በጋራ ተስማቶ ከሰራቸው ስራዎች መካከል የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አንዱ ነው ያሉት ከንቲባዋ፥ ሁላችንም በተባበረ ክንድ ችግኞቻችን በመትከል ታሪክ ልንሰራ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኞች የመትከል መርሐ ግብር በመላው ኢትዮጵያ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.