Fana: At a Speed of Life!

የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች አስታራቂ እና የፍቅር ቃል በማስተላለፍ እንዲተጉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች አስታራቂ እና የፍቅር ቃል በማስተላለፍ እንዲተጉ ጥሪ አቀረበ።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች ከሐምሌ 30 እስከ ነሐሴ 2 ቀን 2017 ዓ.ም በጾምና በጸሎት እንዲያሳልፉ ካውንስሉ መልዕክት አስተላልፏል።

የጥፋት መሣሪያዎችን በማስቀመጥ ልዩነትን በውይይት ለመፍታት እና ግጭትን ለማስወገድ ፈቃደኛ መሆን እንደሚገባ ካውንስሉ አስገንዝቧል።

የካውንስሉ ዋና ፀሐፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ በሰጡት መግለጫ፤ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚንቀሳቀሱ ወገኖች ህብረተሰቡ ይበልጥ ተቀራርቦና ተከባብሮ በሰላም እንዲኖር መስራት አለባቸው ብለዋል።

በመሆኑም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ህብረተሰቡ ከድህነት እንዲላቀቅ መስራት እንደሚገባቸው ገልጸው፤ አስታራቂና የፍቅር ቃል በማስተላለፍ ሊተጉ ይገባል ነው ያሉት።

የሃይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ጉዳዩ የሚመለከታቸውን በመምከር ለሀገር ሰላምና አንድነት እንዲቆሙ መለኮታዊና ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

የካውንስሉ አባል አብያተ ክርስቲያናት ከሐምሌ 30 እስከ ነሐሴ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ስለሀገራቸው ዘላቂ ሰላምና አንድነት በጾምና በጸሎት እንዲያሳልፉ አስገንዝበዋል።

የወንጌል አማኞች አብያተ ከርስቲያናት ከዚህ በፊት ሲያደርጉት እንደነበረው የጳጉሜን ቀናት ስለ ሀገር ሰላም፣ ስለ ሕዝብ ፍቅርና አንድነት እንዲሁም ዕድገት እንዲጸልዩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በነፃነት ፀጋይ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.