በኦሮሚያ ክልል ለመኸር እርሻ የሚሆን የአግሮ ኬሚካል ግብአት እየቀረበ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ለመኸር እርሻ የሚሆን የአግሮ ኬሚካል ግብአት በሁሉም ዞኖች እየቀረበ ነው አለ የክልሉ ግብርና ቢሮ፡፡
በቢሮው የግብርና ግብአት ፍላጎትና አቅርቦት ዳይሬክተር አቶ ታከለ ቁሩንዲ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት፥ በክልሉ ለመሀር እርሻ 5 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር ጸረ አረምና ጸረ ተባይ ኬሚካል ለማስገባት ታቅዶ እየተሰራ ነው።
እስካሁንም 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ሊትር መገዛቱን ገልጸው፥ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ጸረ አረም ኬሚካል ተሰራጭቷል ብለዋል።
ጸረ አረም ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፥ የአቅርቦት እጥረት ባለመኖሩ አርሶ አደሩ ደረጃውን የጠበቀ ኬሚካል ከህብረት ስራ ማህበራትና ፌዴሬሽኖች በመግዛት እንዲጠቀም አሳስበዋል።
በትዕግስት አብረሃም