የሐረሪ ክልል በተከሰተው የዝናብ ዕጥረት ያጋጠመውን የሰብል ጉዳት ለማካካስ እንዲሰራ አቅጣጫ አስቀመጠ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በክልሉ በተከሰተው የዝናብ ዕጥረት ያጋጠመውን የሰብል ጉዳት ለአርሶ አደሩ ድጋፍ በማድረግ በቀጣይ የዝናብ ወቅት ለማካካስ እንዲሰራ አቅጣጫ አስቀምጧል።
የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ሔኖክ ሙሉነህ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፤ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በበልግ እርሻ ስራ እንቅስቃሴ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ሊከሰት የሚችለውን ድርቅ ለመቋቋም ተጠንቶ በቀረበ የመፍትሄ ሀሳብ ላይ መክሯል።
በጥናቱ መሰረት በክልሉ በዘር መሸፈን የነበረበት መሬት በዝናብ እጥረት ምክንያት ሳይሸፈን መቅረቱና በተዘራ ዘር ላይም ውድመት አጋጥሟል።
በዚህም ያጋጠመውን ጉዳት ለማካካስ ከአካባቢው የአየር ንብረት ጋር ተስማሚ የሆኑ በአጭር ግዜ የሚደርሱ ዘሮችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
ከአካባቢው ጋር ተስማሚ የሆኑ ቦሎቄ፣ ስንዴ፣ ስኳር ድንች እንዲሁም በኤረርና ሶፊ ወረዳ ቆላማ ቀበሌዎች መጪዉ ጊዜ ምቹ የምርት ወቅት ስለሚሆን በአጭር ጊዜ የሚደርሱ የማሽላ ዘሮችን በማቅረብ ማሳዎች በዘር እንዲሸፈኑ አቅጣጫ ተቀምጧል ነው ያሉት።
በሌላ በኩል የከብቶች እልቂትን ቀድሞ ለመከላከል በአንዳንድ አካባቢዎች የተገኘዉን ዝናብ በመጠቀም መኖ በማምረት አርሶ አደሩ ምርቱን በቁጠባ እንዲጠቀም ሙያዊ ድጋፍ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡
ከክረምት ወቅት ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ የሚችሉ በሽታዎችን ለመከላከል ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም ምክር ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!