Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ሀገራዊ የምክክር ሂደትን ለማስጀመር የሚያግዝ ውጤታማ ውይይት ተደርጓል – ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በትግራይ ክልል ሀገራዊ የምክክር ሂደትን ለማስጀመር የሚያግዙ ውጤታማ ውይይቶች ተደርገዋል አለ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አመራሮች ከሰሞኑ ወደ ትግራይ ክልል አቅንተው ከተለያዩ አካላት ጋር መምከራቸው ተመላክቷል፡፡

የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ጥበቡ ታደሰ እንዳሉት ፥ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች፣በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ከሲቪል ማህበራት ጋር ውይይት ተካሂዷል።

በነበሩ የውይይት መድረኮች የፕሪቶሪያው ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን፣ ተፈናቃዮች እንዲመለሱና ሌሎች ጥያቄዎች ተነስተዋል ነው ያሉት።

ጥያቄዎቹ እንደ ቅድመ ሁኔታ የተቀመጡ ሳይሆን ተግባራዊ ቢደረጉ የምክክር ሒደቱን በተሻለ ያግዙታል በሚል እሳቤ መነሳታቸውን አስገንዝበዋል፡፡

ክልሉ ለሀገረ መንግስት ግንባታው በጎ ሚና የተወጣ መሆኑን አስታውሰው ፥ በነበረው የምክክር መድረክ በክልሉ ሀገራዊ የምክክር ሂደትን የሚያግዙ ውጤታማ ውይይቶች ተደርገዋል ብለዋል።

የክልሉ ሕዝብ ከሌሎች የሀገሪቱ ሕዝቦች ጋር ችግሮችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣም ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በወንድሙ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.