Fana: At a Speed of Life!

የህዝቡን ፍላጎት መሰረት ያደረገ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የህዝቡን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ለመስጠት በትኩረት እየሰራሁ ነው አለ፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን ከአዲስ አበባ ወደ ጅግጅጋ እየተሰጠ የሚገኘውን የፐብሊክ ትራንስፖርት ልዩ ሀገር አቋራጭ አገልግሎት ተመልክተዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ቀደም ሲል በረዥም የሀገር ውስጥ ጉዞዎች ላይ የሚስተዋሉ የትራንስፖርት ችግሮችን መቅረፍ ያስቻሉ ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡

በአዲስ አበባ አገልግሎት እየሰጡ ከሚገኙ 464 አውቶብሶች በተጨማሪ በ50 ልዩ አውቶቡሶች ከአዲስ አበባ ወደተለያዩ የክልል ከተሞች የትራንስፖርት አገልግሎት እየተሰጠ ነው ብለዋል።

በቀጣይም በዘመናዊ አውቶቡሶች እየተሰጠ የሚገኘውን አገልግሎት ለማሳደግና የህዝቡን የትራንስፖርት ፍላጎት መሰረት ያደረገ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ነው ሚኒስትር ዴኤታው የገለጹት።

ከዚህ በተጨማሪም ከጎረቤት ሀገራት ጋርም በየብስ ትራንስፖርት ለማገናኘት እየተሰራ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡

ሚኒስቴሩ በሶማሌ ክልል የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎትን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በነገው ዕለት ያስጀምራል።

በተስፋዬ ሀይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.