በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ግድፈቶችን ለማረም የሚያስችል ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ግድፈቶችን ለማረም የሚያስችል የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።
”የአገልግሎት ልህቀት ለኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው መድረክ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት አባላትን ጨምሮ በተለያዩ ሴክተር ተቋማት ስር የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ውይይቱን የመሩት የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንቶች አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና አቶ አደም ፋራህ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የምክር ቤቱ አባላትና የሴክተር ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ለቀልጣፋና ዘመኑን ለዋጀ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የበኩላቸውን አስተዋጽፆ ማበርከታቸውን እንዲቀጥሉ በመድረኩ ላይ ተነስቷል፡፡
በቀጣይ በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፎች የተሳካ የአገልግሎት አሰጣጥ እውን ይሆን ዘንድ አመራሩ በመፍጠንና መፍጠር መርህ ተግባራትን መከወን እንደሚገባው ተገልጿል።