Fana: At a Speed of Life!

የትራምፕ እና ፑቲን የአላስካ ቀጠሮ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሩሲያ ዩክሬኑ ጦርነት ዙሪያ መክረው መፍትሄ ላይ ለመድረስ በአላስካ ተገናኝተው ለመምከር ቀጠሮ ይዘዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ዳግም ወደ ነጩ ቤተ መንግስት ከተመለሱ በኋላ ለማድረግ ቃል ከገቧቸው ፖለቲካዊ ውሳኔዎች አንዱ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነትን ማስቆም ነው፡፡

ይህንን ቃላቸውን ወደ ተግባር ለመቀየር ባለፉት ወራት እሳቸው እና ዲፕሎማቶቻቸው የሩሲያ ዩክሬንን ጦርነት ለማሰቆም ብርቱ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

የአሸማጋይነት ሚናቸውን ሲወጡ የቆዩት ፕሬዚዳንት ትራምፕ እና ዲፕሎማቶቻቸው በቱርክ ኢስታንቡል የተደረገውን የሶስት ዙር የሩሲያ እና ዩክሬን ድርድር በማመቻቸት ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡

ምንም እንኳን የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ ባይቻልም ሀገራቱ በሺዎች የሚቆጠሩ የጦር እስረኞች ልውውጥ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት በማድረግ ተተግብሯል።

በኢስታንቡል ካደረጉት የሶስት ዙር ድርድር በኋላ ሩሲያ እና ዩክሬን ወደ ከፋ ጥቃት መሰነዛዘር ገብተዋል፡፡

ይህን ጦርነት ለማስቆም ዶናልድ ትራምፕ የ10 ቀን የተኩስ አቁም ስምምነት ያቀረቡ ሲሆን በዩክሬን ዘንድ አዎንታዊ ምላሽ ሲያገኝ ሩሲያ ግን የፕሬዚዳንቱን የተኩስ አቁም ጥሪ ጆሮ ዳባ ብላለች፡፡

በተለይም የሩሲያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዲሚትሪ ሜድቬዲቭ “አሜሪከ እጃችንን መጠምዘዝ አትችልም” ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የተናደዱት ፕሬዚዳንት ትራምፕ፤ ሁለት የኑክሌር ሰርጓጅ መርከቦችን ወደ ሩሲያ ድንበር እንዲጠጉ በማድረጋቸው ሀገራቱ ፖለቲካዊ ውጥረት ውስጥ ገብተው ቆይተዋል፡፡

ይሁን እንጂ የዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ዊትኮፍ ወደ ሞስኮ አቅንተው ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር ውይይት በማድረግ ቆይታቸውን በተመለከተ ለፕሬዚዳንት ትራምፕ ሪፖርት አድርገዋል፡፡

በዚህም በመጪው አርብ ፕሬዚዳንት ትራምፕ እና ፕሬዚዳንት ፑቲን ተገናኝተው በሩሲያ ዩክሬኑ ጦርነት ዙሪያ ለመምከር ሁለቱ ሀገራትን በምታዋስነው አላስካ ግዛት ቀጠሮ ይዘዋል፡፡

የሁለቱ መሪዎች የፊት ለፊት ግንኙነት የዓለምን ጂኦፖለቲካ ተፅዕኖ ውስጥ የከተተውን የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ወደ ሰላማዊ ድርድር ሊያመጣ ይችላል መባሉን ቢቢሲ፣ ዘጋርዲያን እና አርቲ ዘግበዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.