ከ1 ሚሊየን በላይ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የምስክር ወረቀት ወሰዱ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5 ሚሊየን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና እስካሁን ከ1 ሚሊየን በላይ ወጣቶች ሥልጠናውን በማጠናቀቅ የምስክር ወረቀት ወስደዋል አለ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፡፡
በሚኒስቴሩ የዲጂታል ኢኮኖሚ ሥርዓት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ስዩም መንገሻ እንዳሉት ÷ ኢትዮ ኮደርስ የወጣቶች የቴክኖሎጂ ክህሎት በማሳደግ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ዲጂታል ኢኮኖሚ ዕውን ለማድረግ ያስችላል፡፡
የ5 ሚሊየን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መርሐ ግብር በታቀደው መሰረት እየተከናወነ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል፡፡
አሁን ላይ በመላ ሀገሪቱ ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን እየተከታተሉ መሆኑን ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
ከእነዚህ ውስጥም ከ1 ሚሊየን በላይ የሚሆኑት ሥልጠናውን በሚገባ አጠናቅቀው የምስክር ወረቀት ወስደዋል ነው ያሉት፡፡
አቶ ስዩም ወጣቶች የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ ማሳለጥ የሚያስችለውን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና እንዲወስዱም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ