Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና አሜሪካ ሕገ ወጥ የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶችን ለመቆጣጠር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ሕገ ወጥ ድንበር ተሻጋር የገንዘብ ማስተላለፊያ ግብይቶችን መከላከልና መቆጣጠር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል፡፡

በዚህም በገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶች ላይ በሚደረገው ቁጥጥር ያላቸውን ትብብር ለማጠናክርና የገንዘብ ዝውውሩ በመደበኛ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ መከናወኑን ማረጋገጥ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተወያይተዋል።

በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ይበልጥ ማሻሻል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውንም ባንኩ ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.