Fana: At a Speed of Life!

የእናት ጡት ወተት ለጤናማ ትውልድ መሰረት ነው…

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጤናማ ትውልድ እንዲፈጠር ህጻናት እስከ ስድስት ወር ድረስ ካለምንም ድብልቅ የእናት ጡት ወተት ማግኘት አለባቸው አሉ በጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥነ ምግብ ባለሞያ ጎባኔ ዴአ።

የእናት ጡት ለህጻናት ያለውን ጠቀሜታ በማስገንዘብ ረገድ እናቶች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች የቤተሰብ አባላት የራሳቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው አስረድተዋል።

ባለሞያዋ ከፋና ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት ÷ እናቶች እንደወለዱ በመጀመሪያ የሚገኘውን እንገር የተሰኘ የጡት ወተት ለህጻኑ በመስጠት የህጻኑን ጤንነት መጠበቅ አለባቸው።

ጡት ማጥባት ለሕጻናት ሁለንተናዊ ጤንነት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው፥ ጤናማ ትውልድ እንዲፈጠር የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ወሳኝ ጊዜያት ናቸው ብለዋል።

ማንኛዋም እናት ልጇን ከወለደችበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስት ወር ድረስ ካለምንም ድብልቅ የጡት ወተቷን ብቻ መስጠት እንዳለባትም ነው ያስገነዘቡት።

ከስድስት ወር በኋላም ህጻኑ ሌላ ምግብ እየተመገበ በተጨማሪ እስከ ሁለት ዓመት ድረስ የእናት ጡት ወተት ማግኘቱ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የእናት ጡት ወተት ለህጻናት መስጠት የልጇንም ሆነ የእናቲቱን ጤንነት በመጠበቅ ህጻኑ የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኝ ያስችለዋል ነው ያሉት።
ይህንን ክፍተት ለማስወገድና አስፈላጊውን ግንዛቤ ለመፍጠር በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሐምሌ 25 እስከ ለነሐሴ 1 ድረስ የጡት ማጥባት ሳምንት በተለያዩ ክንውኖች እንደሚከበር ጠቁመዋል።

በጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥነ ምግብ ባለሞያ የሆኑት ጎባኔ ዴአ ከፋና ፖድካስት ጋር የነበራቸውን ቆይታ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ –

በብርሃኑ አበራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.