የውጭ ምንዛሪ ስርዓቱ በገበያ መመራቱ ከባንክ ውጪ የሚላከውን ገንዘብ እያስቀረ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ የውጭ ምንዛሪ ስርዓቱ በገበያ እንዲመራ መደረጉ አብዛኛው የውጭ ምንዛሬ በባንኮች በኩል እንዲላክ አስችሏል አሉ።
ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሬሚታንስ ከሰባት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷንም ገልጸዋል።
ይህም በ2016 ዓ.ም ማብቂያ ላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ወደተግባር በመግባቱ መሆኑን ጠቅሰው፤ የውጭ ምንዛሪ ስርዓቱን በገበያ እንዲመራ መደረጉ ከባንክ ውጪ የሚላከውን ገንዘብ በመቀነስ አብዛኛው በባንኮች እንዲላክ አድርጓል ብለዋል።
ካለው አቅም አንጻር ከዚህ በላይ መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ መቀመጡን ገልጸው፤ በዚህም በተያዘው በጀት ዓመት ስምንት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት መታቀዱን መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ዳያስፖራው ህጋዊ መንገድን ተከትሎ ወደ ሀገር ቤት ገንዘብ እንዲልክ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ፣ ከኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች ጋር በመሆን የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ አመልክተዋል።
ዳያስፖራው በባንክ ስርዓት ሬሚታንስ መላኩ ገንዘቡ አስተማማኝነት እንዲኖረውና አጭበርባሪዎች እጅ እንዳይወድቅ የሚያደርግ መሆኑ ትልቅ ጠቃሜታ እንዳለው ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለጹት።
ለሬሚታንስ መላኪያ ተብሎ ዳያስፖራው ይከፍለው የነበረውን ክፍያ ባንኮች በመሸፈን ማበረታቻ እያደረጉ እንደሆነ ገልጸው፤ ዳያስፖራው ዋስትና የሚሰጠውን ህጋዊ የመላኪያ አማራጭ እንዲጠቀም ጥሪ አቅርበዋል።
ዳያስፓራው https://www.unite.et/ በተሰኘው አማራጭ በመንግስት እና የግል ባንኮች የውጭ ምንዛሬ ሂሳብ ቁጥር በመክፈት ገንዘብ ማስተላለፍ መጀመሩ አካውንት ለመክፈት የነበረውን የወረቀት አሰራር በማስቀረት ትልቅ ለውጥ ማምጣቱን ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከህገ ወጥ የገንዘብ አዘዋዋሪዎች እንዲጠበቁ ያወጣውን ማሳሰቢያ ተከትሎም ከሚሲዮኖች ጋር በመሆን ለዳያስፖራው ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!