በኦሮሚያ ክልል የ32 ሚሊየን መማሪያ መጻሕፍት ሕትመት ሥራ…
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ለ2018 ትምህርት ዘመን ከ32 ሚሊየን በላይ የመማሪያ መጻሕፍትን ለማሳተም ታቅዶ ሥራ ተጀምሯል አለ የክልሉ ትምህርት ቢሮ፡፡
የቢሮው ም/ኃላፊ ቡልቶሳ ኢርኮ (ዶ/ር) ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷ በቀጣዩ ዓመት የመማር ማስተማር ሒደቱን ለማሳለጥ አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡
በዓመቱ ለቅደመ መደበኛ፣1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት የመማሪያ መጻሕፍትን አቅርቦት ለማሟላት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
በዚህ መሰረትም ከ32 ሚሊየን በላይ መጻሕፍትን ለማሳተም ታቅዶ ከአሳትሚ ድርጅቶች ጋር ውል ተይዞ የሕትመት ሥራ መጀመሩን ነው ያስረዱት፡፡
በሌላ በኩል የመማሪያ ክፍሎችን ለትምህርት ዝግጁ የማድረግና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
በክልሉ የተጀመረውን የተማሪዎች ምገባ አገልግሎት አጠናክሮ ለማስቀጠል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በትምህርት ዘመኑ የግብዓት እጥረት እንዳይከሰትና ሁሉም ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው እንዲገኙ አስፈላጊው ክትትል እንደሚደረግም አመልክተዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!